በኢትዮጵያ የሰሞንኛው ወታደራዊ ግጭቶች አንድምታ...

አቶ ክቡር ገና እና አቶ ብርሃነ መዋ

“... ለጠቅላላው ሕዝብ ማለት እችላለሁ አስደንጋጭ እና አስቸጋሪ ጊዜ እንደሆነ ነው። ... እንዲህ ያለ ጦርነት ... በክልልና በፌደራል መንግሥት መሃከል ይካሄዳል’ ብሎ የጠበቀ ያለ አይመስለኝም።” አቶ ክቡር ገና ከአዲስ አበባ። ”... የተገለጹትን ማስረጃዎች (ተመርኩዤ) ስመለከተው ግን ከመነሻው አንድ የክልል መንግስት ልክ እንደ አገር ጦር መሳሪያ ማከማቸት፤ መመልመል እና ለጦርነት መዘጋጀት ሲጀምር ከዛ ነው ጦርነት የተጀመረው ማለት ነው።” አቶ ብርሃነ መዋ።

ትኩረት፦ የሰሞንኛው ወታደራዊ ግጭቶች አንድምታ፤ ዘውግ ለይተው የሚነጣጠሩና ተደጋግመው በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች መንስኤ፥ ዘላቂ መፍትሄ እና ቀጣዩ መንገዶች።

በሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል በፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል በመካሄድ ላይ ያለውን ውጊያ ጨምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መንስኤና ወደፊት ሊያራምዱ የሚችሉ አማራጮችን ጭምር ለማየት የሚጥር ውይይት ነው።

ተወያዮች አቶ ክቡር ገና ከአዲስ አበባ እና አቶ ብርሃነ መዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ናቸው።

የውይይቱን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የሰሞንኛው ወታደራዊ ግጭቶች አንድምታ - ክፍል አንድ

Your browser doesn’t support HTML5

የሰሞንኛው ወታደራዊ ግጭቶች አንድምታ - ክፍል ሁለት