“መግደልና ማሰር እንዲሁም መብትን ማቀብ መፍትሄ አይሆንም″ አምነስቲ ኢንተርናሽናል

  • ሔኖክ ሰማእግዜር

ፎቶ ፋይል

ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላለፉት አስር ቀናት እየተዳደረች ነው።

በኢትዮጵያ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ሲካሄዱ የሰነበቱ ተቃውሞዎችና ሁከቶችን ተከትሎ መንግስት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ የዜጎችን መብት ከመገደብ አልፎ ዘለቄታ ያለው ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን አይፈጥርም ሲል አንድ የመብት ድርጅት አስታወቀ።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የብዙሃን ድምጽ የሚሰማበትና፤ ዜጎች እራሳቸውን የሚመሩበት ስርዓት መፍጠር እንጂ በዜጎች ላይ ግድያ መፈጸምና ማሰር እንዲሁም ሰፊ የመብት ዕቀባ ስርዓት ማስፈን መፍትሄ አይሆንም ብሏል።

የአምነስቲን የኢትዮጵያ መረጃ አጠናቃሪ አቶ ፍስሃ ተክሌን ሔኖክ ሰማእግዜር አነጋግሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

″በዜጎች ግድያ መፈጸምና ማሰር የመብት ዕቀባ ስርዓት ማስፈን መፍትሄ አይሆንም″ አምነስቲ ኢንተርናሽናል