የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ከአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚና ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

Your browser doesn’t support HTML5

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ከአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚና ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ሃገሪቱን ወደ አንድ መድረክ ለማምጣት ኢትዮጵያ ለምታደርገው ሰላማዊ ምክክር አሜሪካ ድጋፍ እንደምሰጥ አስታወቀች። በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ቴሪስ አን ጄከብሰን ባህር ዳር ላይ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በኢትዮጵያ የቻይናንም አምባሳደር ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ከሁለቱም ዲፕሎማቶች ጋር ያደረጉት ውይይት ፍሬያማ እንደነበር ገልፀዋል።