የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ችግሮችን በውይይት ብቻ እንዲፈቱ መንግሥት አሳሰበ

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ችግሮችን በውይይት ብቻ እንዲፈቱ መንግሥት አሳሰበ

ከሰሞኑ በትግራይ ክልል በኩል በአማራ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚታየው አዝማሚያ፣ የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት የሚጥስ ነው፤ ሲሉ፣ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ተናገሩ።

የአማራ እና የትግራይ ክልሎች፣ በመግለጫ እርስ በርስ ከመወቃቀስ ይልቅ፣ ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ እና በድርድር ብቻ መፍታት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ በበኩላቸው፣ ትንኮሳ የፈጸሙት የአማራ ሚሊሻዎች ናቸው፤ በማለት ወንጅለዋል። ይኸውም፣ ፌደራል መንግሥቱ “አከራካሪ” እያለ በሚጠራቸው አካባቢዎች የተመሠረቱ አስተዳደሮች እንዲፈርሱና ታጣቂዎችም ትጥቅ እንዲፈቱ ለማድረግ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ በማሰብ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡

አስተዳደራቸው እና ሕዝቡ ሰላማዊ መንገድን ብቻ እንደሚመርጥ የገለጹት አስተዳዳሪው፣ ሕዝበ ውሳኔ የሚካሔደውም “በምርጫ የተመሠረተ መንግሥት ሲኖር ነው፤” ሲሉ ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።