የአማራ ክልል መንግሥት ክስ እና የህወሓት ምላሽ

ህወሓት ጦርነት በከፈተባቸው አካባቢዎች ሁሉ አስክሬን ጭኖ ሲወስድ የነበረው ጅምላ ግድያ ተፈፀመብኝ በማለት ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማደናገር እንደሆነ ቀድመን እናውቅ ነበር ሲል የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት የሰበሰበውን አስክሬን ከሰሞኑ ወንዝ ዳር በመጣል መንግሥት ግድያውን እንደፈፀመ የሚያስመስል የተሳሳተ መረጃ ማሰራጨቱ የህወሓት የተለመደ ሴራ ነው ሲሉ ነው የአማራ ክልል መንግሥት ቃል አቀባይ ግዛቸው ሙሉነህ ያስትወቁት።

የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ማስጠንቀቂያ አንድ በሚል ከሁለት ሳምንታት በፊት ባወጣው መረጃ ህወሓት ጅምላ ጭፍጨፋ ተፈፀመ የሚል ዘመቻ ለመጀመር መዘጋጀቱን ገልጾ ነበር።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ክአሜሪካ ድምፅ ጋር ባደረጉት ቆይታ "የክልላችን ልዩ ሃይል ከወልቃይት የሚወጣው በመቃብራችን ላይ ነው" በማለትም እየቀረቡ ያሉ ጥሪዎችን እንደማይቀበሉ ተናግረዋል።

ይህንን አስመልክቶ በዩናይትድ ስቴትስ የትግራይ ኃይሎች ተጠሪ አምባሳደር ፍስሃ አስገዶም አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የአማራ ክልል መንግሥት ክስ እና የህወሓት ምላሽ