በምዕራብ አማራ በፍኖተ ሰላም ከተማ ዛሬ በተፈጠረ ግጭትና የአንድ ሰው ቤት ለማቃጠል ሌሎች ሰዎች ሙከራ አደረጉ በተባለበት ወቅት ከባለቤቱ በተሰጠ ምላሽ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱና ቤቱ መቃጠሉን የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ዋሺንግተን፤ ዲ.ሲ. —
Your browser doesn’t support HTML5

በጎንደር ከተማ ትናንት የተጀመረው ሥራ የማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉና በባሕር ዳር ደግሞ በአድማ ላይ ተሣትፋችኋል የተባሉ የንግድ ድርጅቶች እየታሸጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጎንደር ውስጥ ወደ አንገረብ ማረሚያ ቤት ትናንት የሄዱ የመከላከያ ሰዎች በዚያ ላሉ ሰዎቻቸው ደመወዝ ለመክፈል እንጂ በቁጥጥር ሥር ያሉትን የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አመራር አባሉን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴን ወደ ሌላ ሥፍራ ለመውሰድ እንዳልነበረ የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አመልክተዋል፡፡
በርከት ላሉ ተጨማሪ መረጃዎች የጎንደርና የባሕር ዳር ከተሞች ነዋሪዎች፣ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለገሠ ተፈረደኝ እና የአማራ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ቃሎችና ቃለ-ምልልሶች የተካተቱባቸውን ከዚህ ጋር የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡