በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ እንደኾነ ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል በቀጠለው ግጭት በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ እንደኾነ ተገለጸ

በዐማራ ክልል በመከላከያ ሠራዊቱ እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሔደው የተኩስ ልውውጥ እና ግጭት፣ የበርካታ ንጹሐን ሰዎች ሕይወት እያለፈና በደረሱ ሰብሎችም ላይ ጉዳት እደረሰ እንደሚገኝ፣ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማና ዙሪያው አካባቢ ከትናንት በስቲያ በጀመረውና እስከ ትናንት ዕኩለ ቀን በቆየው የተኩስ ልውውጥ ሲቪሎች ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የእናርጅ እናውጋ ወረዳ፣ በደቡብ ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ እና ከክልሉ ርእሰ መዲና ባሕር ዳር ከተማ 18 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኘው መሸንቲ፣ ጉዳት እንዳስከተሉ የተገለጹት የትጥቅ ግጭቶቹ የተካሔደባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡

አስተያየት ሰጪው፣ የመከላከያ ኀይሉን ተጠያቂ ያደርጋሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ፣ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር እስከ አሁን የሰጠው ማስተባበያም ኾነ ማረጋገጫ የለም፡፡ ይኹንና፣ ሰሞኑን በደብረ ማርቆስ ከተማ በተደረገው ሕዝባዊ ውይይት ላይ፣ ሕገ ወጥ ተግባር የሚፈጽሙ የመከላከያ አባላት ካሉ ርምጃ እንደሚወሰድ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡