ትናንትና ከትናንት በስቲያ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ አካባቢና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አጎራባች ቀበሌዎች ተፈጥሮ የነበረው ውጥረት እየተረጋጋ መምጣቱን የፀጥታ ኃይሎችና ኅብረተሰቡ ገልፀዋል፡፡
ደሴ —
የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ ተኩሱን የሚተኩሱት መትረየስና አልሞ መች መሳሪያ የያዙ ታጣቂ ናቸው ማለታቸውን ጠቅሰን ትናንት በምሽቱ የዜና ዕወጃችን ማሰማታችን ታወቃል፡፡
ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ በወረዳው የካራቆሬ አካባቢ ኗሪ ውጥረቱ እንዲያገረሽ የሚያደርጉ አዝማሚያዎች ስለሚስተዋሉ በአካባቢው አስተማማኝ የፀጥታ ኃይል በአካባቢው እንዲሰፍር ጠይቀዋል፡፡
በሌላው የወረዳው ክፍል በማጀቴ አካባቢም ዛሬ ማለዳ የጥይት ድምፅ መሰማቱን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5