በባሕርዳር ከተማ የታሰሩ ሰዎች የአማራን ጉዳይ ስላነሱ ነው ሲሉ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገለጹ

የኢትዮጵያ ካርታ

በባሕርዳር ከተማ ውስጥ በአንድ ላይ የነበሩ የዩኒቨርስቲ ምሑራን፣ የመንግሥትና የግል ጋዜጠኞችና ሌሎች ባለሞያዎች በአጠቃላይ 19 ሰዎች ቅዳሜ መጋቢት 15/2010 ዓ/ም መታሰራቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

ግለሰቦቹ የአማራ ሕዝብ እየተፈፀመበት ላለለው የመብት ጥሰትና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መረሳት ተወካይ አካል ያስፈልገዋል በሚል ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠየቃቸውን መስፈርት ለማሟሟላት በመንቀሳቀስ ላይ እንደነበሩም ተናግረዋል። በዕለቱም ስለሚያስፈልጋቸው ነገር ተወያይተው ከጨረሱ በኋላ እራት እየበሉ መታሰራቸን ነው የገለፁት። የአማራ ክልል ቃል አቀባይ ስልካቸው ስለማይነሳ ልናገኛቸው አልቻልንም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በባሕርዳር ከተማ የታሰሩ ሰዎች የአማራን ጉዳይ ስላነሱ ነው ሲሉ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገለጹ