የአማራ ክልል ግጭት በሰላም እንዲፈታ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና እንዲያደርግ ካውንስሉ ጠየቀ

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ

Your browser doesn’t support HTML5

የአማራ ክልል ግጭት በሰላም እንዲፈታ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና እንዲያደርግ ካውንስሉ ጠየቀ

ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ፣ የአማራ ክልል ግጭት ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ በተፋላሚ ኃይሎች ላይ ጫና እንዲፈጥሩ የክልሉ የሰላም ካውንስል ጠይቋል፡፡

በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ መካከል በሚደረገው የግጭት ዐውድ ውስጥ የሚፈፀመው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን የገለፀው ኢሰመኮ ግጭቱ በውይይት እንዲፈታ ከትላንት በስቲያ መጠየቁ ይታወቃል፡፡

የአማራ ክልል የሰላም ካውንስልሰብሳቢ ያየህይራድ በለጠ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ካውንስሉ መንግሥትን እና ፋኖን ወደ ድርድር ለማምጣት የማመቻቸት ኃላፊነቱን በመቀጠል ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋራ በመነጋገር ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ካውንስሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ከዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጋራ ንግግር ማድረጉን እና ጫና እንዲፈጥሩ መጠየቁን ተናግረዋል፡፡