በአማራ ክልል በሦስት ወር ውስጥ 37 ሰዎች በወባ በሽታ ሕይወታቸው ማለፉን ከልሉ አስታወቀ

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል በሦስት ወር ውስጥ 37 ሰዎች በወባ በሽታ ሕይወታቸው ማለፉን ከልሉ አስታወቀ

በአማራ ክልል በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት አስፈላጊ ቁጥጥር እና ክትትል ባለመደረጉ፣ በሦስት ወራት ውስጥ 37 ሰዎች በወባ መሞታቸውን፣ በአንድ ሳምንት ብቻ ደግሞ ከ64 ሺሕ ሰዎች መያዛቸውን ክልሉ አስታወቀ።

በኢንስቲትዩት የወባ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ዳምጤ ላንከር ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ600 ሺሕ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል።

የወባ ወረርሽኙ በብዛት ተከስቶባቸዋል በተባሉት ምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢ ጠህናን ወረዳና በባህር ዳር ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎችና የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በቅርቡ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት አስተያየት የወረርሽኙ 70 በመቶ የሚኾነው ስርጭት በ222 ወረዳዎች መኾኑን ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡