የአማራ ክልል ግጭት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ማስከተሉ ተገለፀ

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ

Your browser doesn’t support HTML5

የአማራ ክልል ግጭት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ማስከተሉ ተገለፀ

ከአንድ ዓመት በላይ የቀጠለው የአማራ ክልል ግጭት ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት ማስከተሉን ጥናት ማመልከቱን የክልሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም አስታውቋል።

ፎረሙ ይሄንን ያስታወቀው፣"የሰብዓዊ ምላሽ ስልት በግጭት በተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች" በሚል ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ባዘጋጀው እና ትላንት ይፋ ባደረገው ሰነድ ነው።

ሰነዱ አክሎም “ግጭቱን ተከትሎ በድምሩ ከ 15 ሺህ በላይ ሰዎች የሞት፣ የመቁሰል፣ የአዕምሮና ማሕበራዊ ቀውስ እንደዚሁም የፆታዊ ጥቃት ሰለባ ሆነዋል” በማለት ጠቅሷል።

የፎረሙን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ታፈረ መላኩን ዘጋቢያችን አነጋግራለች።