Your browser doesn’t support HTML5
በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች እና ከእነርሱ ጋራ ግንኙነት አላቸው በተባሉ አካላት ላይ ከወትሮው የተጠናከረ እርምጃ መውሰድ ጀምሬአለሁ ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እና የመከላከያ ሠራዊት በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ እርምጃው እስካሁን ድረስ መለስተኛ ኦፐሬሽን በመውሰድ ችግሩን በሰላም ለመፍታት የተደረገው ጥረት ውጤት ባለማምጣቱ ነው ብለዋል፡፡
በተያያዘ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት፣ ከቅዳሜ ጀምሮ “መንግሥት በአማራ ክልል የዘፈቀደ የጅምላ እስር እያካሔደ ነው” በማለት ወንጅሏል።
ከፋኖ ታጣቂ ቡድን ተወካይ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡
ከመንግሥት በኩልም ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ኬኔዲ አባተ ያስተላለፈው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡