በዐማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ አካባቢ፣ ባለፈው ሰኞ የተቀሰቀሰው ውጊያ፣ ዛሬም ቀጥሎ እንደዋለ፣ የአካባቢው የመረጃ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ትላንት ረቡዕ ምሽት በድሮን እንደኾነ በገለጹት ከባድ መሣሪያ፣ የሰው ሕይወት ማለፉንና የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል፡፡
SEE ALSO: ለቀናት በቀጠለው የፈረስ ቤት ግጭት ከባድ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት እንደደረሰ ተገለጸውጊያው ዛሬም ቀጥሎ እንደዋለ ምንጮቹ ጠቁመው፣ ከከባድ መሣሪያ ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል፣ በርካቶች በዱር እና በገደል አካባቢዎች ለመደበቅ እንደተገደዱ ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።