በአማራ ክልል የተፈናቃዮች ቁጥር 1.7 ሚሊዮን ደርሷል ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል የተፈናቃዮች ቁጥር 1.7 ሚሊዮን ደርሷል ተባለ

በአማራ ክልል ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የተፈናቃዮች ቀጥር እጅግ መጨመሩን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

የክልሉ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ኮሚሽን ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፀው በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች እየተፈናቀለ ያለው ህዝብ ከ1.7 ሚልየን በላይ የደረሰ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ በጦርነት ብቻ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ750 ሺሕ መብለጡን አስታውቋል።

በቂ የሆነ የሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ እንዳልሆነ የገለፁት የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ እያሱ መስፍን በተለይ ህወሃት በተቆጣጠረባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረስ እንዳልተቻለ ገልፀዋል።