Your browser doesn’t support HTML5
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ፣ ብልባላ ከተማ ላይ ኅዳር 23 እኩለ ሌሊት ላይ ተፈጸመ በተባለ የድሮን ጥቃት የ83 ዓመት አዛውንት መነኩሴ እናታቸው መገደላቸውን የሟች ቤተሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
ተሰነዘረ በተባለው ጥቃት ሁለት የህክምና ባለሞያዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱንም የአካባቢው ነዋሪዎችና አንድ የጤና ባለሞያ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ኅዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ ዙሪያና አካባቢው በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ለሰዓታት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ደረሰ ስለተባለው የህይወትና የአካል ጉዳት ከክልሉ፣ ከአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ከጤና ተቋማት ኃላፊዎች መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።