በዐማራ ክልል በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ እንቅስቃሴ እንደተገደበ ነዋሪዎች ገለጹ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በዐማራ ክልል በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ እንቅስቃሴ እንደተገደበ ነዋሪዎች ገለጹ

ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር መጨረሻ አንሥቶ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ሥር በሚገኘው የዐማራ ክልል ልዩ ልዩ አካባቢዎች፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭቱ እና የተኩስ ልውውጡ ቀጥሎ እንቅስቃሴያቸውን እያወከው እንደኾነ፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

ከትላንት እሑድ ጀምሮ፡- የምሥራቅ ጎጃም፣ የምዕራብ ጎጃም፣ እንዲሁም የሰሜን ሸዋ ዞኖች ከተሞች እና ዙሪያቸው፣ የተኩስ ልውውጡ የቀጠለባቸው እንደኾኑና ሰላማውያን ሰዎችም እንደተጎዱ፣ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ከከተሞቹ አንዱ በኾነው በደብረ ማርቆስ የተቀናጀ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዲሬክተር አብዬ ዘለቀ፣ በተኩስ ልውውጡ ጉዳት ደርሶበት ለሕክምና ሆስፒታል የገባ ሰው እንደሌለ ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።