በጅጋ ከተማ በቀጠለ ግጭት ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መዲና ባህር ዳር ከተማ

በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ጅጋ ከተማ፣ ከትላንት በስቲያ እሑድ፣ በመንግሥት እና በፋኖ ቡድን ታጣቂዎች መካከል የተነሣውን ግጭት ተከትሎ፣ ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።

ጅጋን ከተማና የአካባቢው ሕዝብ በመወከል የተመረጡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በበኩላቸው ሲቪሎች መገደላቸውን ገልጸው፤ ጉዳዩን ለአገር ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

በጅጋ ከተማ በቀጠለ ግጭት ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ፣ ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። ከክልሉ እና ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

አስቴር ምስጋናው የአካባቢውን ነዋሪዎች እና የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስተያየት ጠይቃ ያጠናቀረችውን ዘገባ እንደሚከተለው ታቀርበዋለች።