በልዩ ዞኑ ባቲ ወረዳ በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

በልዩ ዞኑ ባቲ ወረዳ በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ ወረዳ በሦስት ቀበሌዎች በያዝነው ሚያዝያ ወር በተከሠተው የኮሌራ ወረርሽኝ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን፣ የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ፡፡

የኢንስትቲዩቱ ዋና ዲሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ በወረዳው በሦስት ቀበሌዎች በተዛመተው የኮሌራ ወረርሽኝ 162 ሰዎች ሲያዙ፣ ከእነዚህም ውስጥ ሁለቱ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ቀሪዎቹ ወደ ሕክምና ተቋማት ተወስደው በቂ ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደኾነ የገለጹት አቶ በላይ፣ ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ ከክልል እስከ ወረዳ ባሉ ባለሞያዎች በትኩረት እየተሠራ ነው፤ ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።