የዐማራ ክልል ግጭትን ለመፍታት የተቋቋመው የሰላም ምክር ቤት የድርድር ጥረት መጀመሩን አስታወቀ

ፎቶ ፋይል፦ ባህር ዳር፤ ኢትዮጵያ

የዐማራ ክልል መንግሥት በቅርቡ ባዘጋጀው የሰላም ኮንፍረንስ ተሳታፊዎች የተቋቋመው "የሰላም ምክር ቤት"፣ በመንግሥት እና በፋኖ ታጣቂ ቡድን መካከል የሰላም ድርድር ለማድረግ ጥረት መጀመሩን አስታወቀ።

የምክር ቤቱ አባላት፣ ባለፈው ቅዳሜ በባሕር ዳር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ሊኖር የሚችለውን ድርድር የማሳለጥ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

SEE ALSO: መንግሥት ለሀገራዊ ምክክሩ አስቻይ ኹኔታዎችን እንዲፈጥር ኮሚሽኑ ጠየቀ

የሰላም ምክር ቤቱ፣ በመንግሥት በተዘጋጀ ጉባኤ የተቋቋመ መኾኑን የገለጹ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች፣ በገለልተኛነቱ ላይ ጥያቄ አንሥተዋል። ሌሎች ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የተጀመረው ጥረት ሰላም እንዲያመጣ ምኞታቸው ገልገልጸዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

የዐማራ ክልል ግጭትን ለመፍታት የተቋቋመው የሰላም ምክር ቤት የድርድር ጥረት መጀመሩን አስታወቀ