ሀሙስ መጋቢት 13 የዓለም የውኃ ቀን ተከብሮ ሲውል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ውኃ ለምግብ ዋስትና ያለውን ወሳኝ ሚና በማስገንዘብ የምግብ አቅርቦት ጥያቄ በጨመረ መጠን፣ ለውኃ አቅርቦት የሚኖረው ጥያቄም በዚያው መጠን እንደሚጨምር ገልጿል።
የግብርናና የውሃ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ በዚህ እረገድ ያለው ፈተና ቀላል ባይባልም፣ ሊወጡት የማይቻል ግን አይደለም።
ዛሬ በዓለማችን ያለው የውኃ አቅርቦት ጥያቄ ብርቱ ትኩረትን ጭሯል።
በዓለም ዙሪያ የንጹህ ውሃ አቅርቦትን ለማዳረስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀየሰው የሚሊኒየሙ የልማት ግብ ማሳካቱ እየተገለጸ ባለበት ወቅት፤ የኢትዮጵያ ሁኔታ ምን እንደሚመስል የተቀናበሩ ዘገባዎችን በገጹ ቀኝ አምድ በመሄድ ያዳምጡ።