በስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ ታጋይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ለመከላከያ ምስክርነት ጠርተዋል
ህዝባዊ ወያን ሃርነት ትግራይ በጫካ ትግሉ ወቅት ያሳለፈውን ትግል በሶስት ተከታታይ መጻህፍት በትግርና “ገሃድ I, II, III” በሚል ያሳተሙ የቀድሞ ታጋይ በስም ማጥፋት ወንጀል ተከሰው በፍርድ ቤት ጉዳዩን በመከታተል ላይ ናቸው።
ደራሲው አቶ አስገደ ገ/ስላሴ የመከላከያ ምስክር እንዲሆኑላቸው የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትንና ነባር የህወሃት አባላትን በመቀሌ ፍርድ ቤት ለእማኝነት ጠርተዋል።
ተከሳሹ የምስክሮችን የውሎ አበልና የመጓጓዣ ወጭ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፤ “አቅም ስሌለኝ ፍትህ ሊጓደልብኝ ይችላል” ሲሉ አቶ አስገደ ለቪኦኤ ገልጸዋል። ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ