የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ ክልል እራሱን በሳት አቃጥሎ የሞተው መምህር ‘እብድ’ ነበር አለ

መምህሩን የሚያውቁ ሰዎች ጤናማ መሆኑን ገልጸው፤ ለጓዶቹ ተቆርቋሪና የታሰሩን ጠያቂ ነበር ብለዋል

በደቡብ ክልል ዳዉሮ ዞን ተርቻ ከተማ እራሱ ላይ እሳት ለኩሶ ሕይወቱ ያለፈዉ መምህር የፓለቲካ ተቃዋሚ ሳይሆን የአምምሮ ሁከት ነበረበት ሲል የኢትዮጵያ መንግስት መረጃ ዋልታ ህዳር ሰባት ዘግቦል።

የአሜሪካ ድምጿ ትዝታ በላቸዉ፣ ይህወቱ ያለፈዉ የቀድሞ መምህር ቆስሎ ሃኪም ቤት ሲከታተሉት የቆዩትን ዶክተርና የአካባቢዉን ነዋሪ አነጋግራለች። ዛሬም ከአካባቢዋ ያነጋገርናቸዉ ነዋሪዎች ግን በራሱ ላይ እሳት የለኮሰው የቀድሞ መምህር ጤናማ ነበር ይላሉ።

ዋልታ የመረጃ ማእከል ባለፈዉ አርብ ህዳር አንድ እራሱን በእሳት አጋይቶ ከሁለት ቀናት ሆስፒታል ዉስጥ ቆይታ በሁዋላ ህዳር አራት ሕይወቱ ያለፈዉ የየኔ ሰዉ ገብሬ የፖለቲካ ተቃዋሚ ሳይሆን የአእምሮ ሁከት ነበረበት ሲል በትላንት ዘገባዉ አስነብቦል።

ማእከሉ የተረቻ ሆስፒታል ዋና ሃላፊ መብራቱ ማሰቦ የዳዉሮ ዞን ፓሊስ አዛዥና፥ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ እስራኤል አታአራንና እንዲሁም የሙዋቹን እህት ወይዘሮ ታደለች በቀለን ዋቢ አድርጎ፣ ነዉ እራሱን የሰዋዉ የኔሰዉ የአምምሮ ህመምተኛ እንጂ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮና በሌሎች የዜና አዉታሮች እንደተዘገበዉ የፍትህ መጉዋደልና ብልሹ አስተዳደርን በመቃወም አልነበረም ሲል የዘገበዉ።

ዛሬም እዉነቱን ለማጣራት ወደ አካባቢዉ ስልክ ደዉለን መምህር የኔነህን በቅርብ የሚያዉቅና ተቃጥሎ ተርቻ ሆስፒታል በተኛባቸዉ ሁለት ቀናት ያከሙትን ባለሙያ በጉዳዩ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበው፤ ሆስፖታሉ የያዘው አቋም ስላለ ዘጋቢያችንን ወደዚያ የሆስፒታሉ አቋም መርተዋል።

ቃለ ምልልስ የሰጡንን ጥቃት እንዳይደርስባቸው የሰጉ ያካባቢው ነዋሪዎች መነሻዉ የዋካ ከተማ እንደቀድሞ የወረዳ አስተዳደር እንዲሆን የአካባቢዉ ህዝብ በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረቡ፥ የሃያ ዘጠኝ ዓመት እድሜ የነበረዉ የኔሰዉ ገብሬ በዚህ ሳቢያ በዋካ ተከማ ታስረዉ ከነበሩ ወጣቶች አንዱ እንደነበርና ከተለቀቀም በሁዋላ ለተቀሩት ባልደረቦቹ መፈታት ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ገልጸዉልናል።

በመጨረሻም እራሱ ላይ ቤንዝን ህይወቱን ያጠፋዉ ያለመለቀቃቸዉን በመቃወም ነዉ፣ አሁንም ቢሆን ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቅ ወጣቶች በዋካ ከተማ እንደታሰሩ ነዉ ብለዋል።

ምንጩ አክለውም መምህር የኔሰው ጤናማ መሆኑን ገልጸው፤ ለጓዶቹ ተቆርቋሪና የታሰሩን ጠያቂ ነበር ብለዋል።