ማህበሩ በዓመቱ የጐዳናና የማራቶን ሯጮችን አወዳድሮ ነው ማካዑን ለወርቅ ጫማ ሽልማትና እውቅና ያበቃው።
በአትሌቲክስ፥ የዓለምአቀፉ የማራቶንና የረዥም ርቀት ሩጫ ማህበር በያዝነው ዓመት ኬንያዊውን ፓትሪክ ማካዑን የዓመቱ ምርጥ የጐዳና ሯጭ አድርጐ ሰየመ። ማህበሩ በዓመቱ የጐዳናና የማራቶን ሯጮችን አወዳድሮ ነው ማካዑን ለወርቅ ጫማ ሽልማትና እውቅና ያበቃው።
ይህን ታላቅ ሽልማት ካገኙት አሥራ ዘጠኝ ታዋቂ የረዥም ርቀት ሯጮች መካከል ኃይሌ ገብረሥላሴ ሦስት ጊዜ፥ ገዛኸኝ አበራ እና ኬንያውያኑ ፖል ቴርጋትና ሳሚ ዋንጂሩ አንድ አንድ ጊዜ ማግኘታቸው ይታወቃል።
በእግር ኳስ ዜና፥ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፳፭ኛ ሳምንቱን ይዟል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ትላንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በአቻ ውጤት ነጥብ ተጋርቶ መውጣቱ፥ የሊጉን መሪነት ከደደቢት ለመረከብ አስችሎታል። የደረጃ ሠንጠረዡን በ ፵፯ ነጥብ በአንደኛነት ይመራል።
በሌላ ዜና፥ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለብሄራዊ ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል። ይህንኑ አስመልክቶ ከፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ከአቶ መላኩ አየለ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል።
ሳምንታዊውን የስፖርት ቅንብር ቀጥሎ ያድምጡ።