የጂማው የሃይማኖት ግጭት ክዋረጂ በተባለ አክራሪ ድርጅት መቀስቀሱን መለስ ዜናዊ አስታወቁ

  • ቪኦኤ ዜና

በጂማ አካባቢ በአሰንዳቦ ከተማና አካባቢው በሚገኙ ቀበሌዎች በርካታ የወንጌላዊያን ቤተክርስቲያናትንና የአማኞች መኖሪያዎችን ያቃጠለው፤ በአካባቢው የሚንቀሳቀስ አክራሪ የእስልምና ቡድን እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒትር መለስ ዜናዊ አስታወቁ።

ክዋረጂ የተባለ አክራሪ የእስልምና ቡድን በአካባቢው የሀይማኖት መቻቻል እንዳይኖር ይሰብካል ሲሉ አቶ መለስ በትናንትናውለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በመካከለኛው ምስራቅ በተለይ በየመን የሚታየው የጸረ-መንግስት ተቃውሞ ማእከላዊ መንግስቱን ካዳከመ አልቃይዳና የአካባቢው አክራሪ ድርጅቶች እንደሚጠናከሩ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥና በውጭም የኢህ-አዴግን ወደ 20ዓመት የሚጠጋ አስተዳድር ለመጣል የሚደረጉ ጥረቶች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰው። “ይሄ አካሄድ በፍጹም በኢትዮጵያ አይሰራም” ብለዋል። ሆኖም ሙከራ የሚያደርጉ ሰዎች አይኖሩም ማለት አይደለም ብለዋል።