የተገልጋዮቹ ቁጥር በወር እስከ 1ሚሊዮን ድርሷል
ገበሬዎችና የችርቻሮ ነጋዴዎች በስልክ ደውለው አገር አቀፍ የምርት ዋጋን የሚያገኙበት አሰራር በኢትዮጵያ ተጀምሯል።
ከሶስት አመታት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ የምርት ገበያ በሞባይል የቴክስት መልእክትና ከማንኛውም ስልክ በሚደረግ ጥሪ በአራት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬዎችና የቡና ምርት ዋጋን ማወቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ.ር እሌኒ ገብረመድህን ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይሄ የመረጃ አገልግሎት ገበሬዎች በምርት ወቅት የመደራደር ችሎታ እንዲያዳብሩና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ሙሉ ቃለ ምልልሱን ያዳምጡ