የጀርመኗ ከተማ ቦን ላይ ለሁለት ሣምንታት እየተካሄደ ያለው የአየር ንብረት ጉባዔ ነገ፤ ዓርብ ይጠናቀቃል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ ኢትዮጵያ የአርባ አምስት ሚሊየን ዶላር ድጋፍ በቅርቡ አግኝታለች።
በቦኑ ጉባዔ ላይ እያሻቀበ የመጣው የዓለም የብክለት መጠን፣ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያና ምርምር የሚያስፈልገው በጀት በስፋት ከተመከረባቸው መካከል እንደሆነ ታውቋል።
በጉባዔው ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ሁለት ገፅታ ይዛ ተገኝታለች። አንድም የፓሪስ ስምምነት አካል ያልሆነች አሜሪካ፤ አንድም ስቴቶችን፣ ኩባንያዎችና ታዋቂ ግለሰቦችን ያሰባሰበን ቡድን ያካተተች የውሉ አካል እንደሆንን እንቀጥላለን ያለች አሜሪካ።
ቀደም ሲል በተደረሱ ስምምነቶች መሠረት ከዓለም አቀፉ የአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ ተጠቃሚ ሃገሮች አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ለያዘቻቸው የሃምሣ ሚሊየን ዶላር ወጭ የሚጠይቁ የውኃ አቅርቦት፣ ከፆታ ጋር ለተያያዙ ፕሮጀክቶች፣ ድርቅን ለመቋቋም ጉዳይ እና ለመሣሰሉ ሥራዎች የአርባ አምስት ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ባለፈው ጥቅምት ውስጥ ማግኘቷ ታውቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5