ዕውቁ አሜሪካዊ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ግራም ዛሬ በ99 ዓመት ዕድሜያቸው አረፉ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ዕውቁ አሜሪካዊ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ዛሬ በ99 ዓመት ዕድሜያቸው አረፉ።
የሃያኛው ምዕተ ዓመት ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳዳሪ የሆኑ ሰባኪ ተደርገው ይታያሉ።
ቢሊ ግራም በ85 ሀገሮችና ግዛቶች እየተዘዋወሩ ለአሥርት ዓመታት ያህል ከሁለት ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ይሰብኩ በነበረበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱሱን ወደ ላይ ከፍ አድርገው ያወዛውዙ፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ያሰባስበ ስብከት ያደርጉ ነበር።
በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችም ስብከታቸውን በቴሌቪዥንና በሳተላይት ይከታተሉ ነበር። ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ለሰባ ዓመታት ያህል ባካሄዱት ስብከት፣ የሰዎች ችግሮች መልስ የሚያገኙት “በኢየሱስ ክርስቶስ ሲያምኑና ሲቀብሉት ብቻ ነው፡፡” የሚል ዕምነት ነብራቸው።
ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ከአንታርቲካ በሥተቀር በሁሉም አህጉራት እየተዘዋወሩ ሰብከዋል። በሳተላይትም ይታዩ ነበር። በሶቭየት ሕብረትና አጋር በነበሩት ሀገሮች ሰብከዋል።
እአአ በ1994 ዓ.ም በቻይናና ሰሜን ኮርያ ቅዳሴ አካሄደዋል። ከሀገሮቹ የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎችም ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።