ከዩኒቨርሲቲዎችና ኮሎጆች የተመረቁ "ሥራ አጣን" ሲሉ አማረሩ

Ambo University

Ambo University

ከዓመታት በፊት ከተለያዩ የአምቦ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሎጆች የተመረቁ ተማሪዎች ሥራ ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን እየገለፁ ናቸው።

ከዓመታት በፊት ከተለያዩ የአምቦ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሎጆች የተመረቁ ተማሪዎች ሥራ ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን እየገለፁ ናቸው።

የሥራ ዕድሎችን ለማመቻቸት የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴም ተዳክሟል ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በተጨማሪም “የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ይሟገቱ የነበሩ ሦስት ወጣቶች መታሰራቸው አስከፍቶናል” ሲሉ አስተያየታቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ወጣቶች ተናግረዋል።

የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ “ለወጣቶቹ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተጀመረው ጥረት አልተቋረጠም” ሲሉ የአምቦ ከተማ ምክትል ከንቲባ ደግሞ ችግሩን በውይይት እንፈታለን፣ ሥራ ፍጠሩልን በሚል ጥያቄ የታሰረ ወጣት ካለም ይፈታል ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ከዩኒቨርሲቲዎችና ኮሎጆች የተመረቁ "ሥራ አጣን" ሲሉ አማረሩ