የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታ አሰሙ

"በመንገድ ግንባታ ምክንያት የምንኖርበትን የመንግስት ቤት ቶሎ እንድናፈርስ መወሰኑ ቅሬታ አሳድሮብናል" ሲሉ አንዳንድ የአምቦ ከተማ 03 ቀበሌ ነዋሪዎች ተናገሩ:: "ግንባታው ከ100 በላይ አባ ወራዎችን ስለሚያስነሳ ቤት አልባ ያደርገናል" ብለዋል::

የከተማው ከንቲባ ተወካይ አቶ ቱፋ አብዲ "ቤቶቹ እንዲነሱ የተወሰነው የመንገዱ ግንባታ ተቋራጭ የግንባታውን ቦታ ባለማፅዳታችን አቤቱታ በማቅረቡ ነው" ሲሉ ተናግረዋል::

"ከቦታው ለሚነሱ አቅመ ደካሞችና ቤት የመስራት አቅም ያላቸውን ለይተን ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሄ እንሰጣለን" ብለዋል::

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታ አሰሙ