“ኢትዮጵያ ውስጥ ጥላቻና ብጥብጥ ከሚቀሰቅሱ የዳያስፖራ አባላት የተወሰኑት ዩናየትድ ስቴትስ የሚገኙ ናቸው” ሲሉ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ አምባሳደር ተናግረዋል።
አዲስ አበባ —
“ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኙበት ምቾትና ደኅንነት ውስጥ ሆነው እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥላቻና ብጥብጥ ያነሳሳሉ” ብለዋል አምባሳደር ማይክ ራይነር።
ሰሞኑን በተመሣሣይ ጉዳይ ላይ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “ጥላቻና ብጥብጥ ያነሳሳሉ” ያሏቸውን “አንዳንድ” የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት “የእውነት አምላክ ይፍረድባቸው” ሲሉ አማርረዋል።
የሚባሉትን ኢትዮጵያዊያን አስመልክቶ በሁለቱ ሃገሮች መካከል የተደረገ ንግግር ስለመኖር አለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5