ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሚገኘው አማሮ ወረዳ ላይ በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነ የወረዳው አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገለፁ። ስለጉዳዩ መረጃ እንደደረሳቸው የተናገሩት የኦነግ ሥራ አስፈፃሚ አባልና ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ በበኩላቸው “ድርጊቱ የተፈፀመው ‘በኦነግ ሠራዊት ነው፤ አይደለም’ የሚለውን በማጣራት ላይ ነን” ብለዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በአማሮ ወረዳና በምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረውን ግጭት ለማብረድ ከገቡ የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ሦስቱ መገደላቸውንና ሁለት መቁሰላቸውንም የተናገሩት አስተዳዳሪው አቶ አማኑዔል አብደላ “ታጣቂዎቹም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሰዎች ስለ መሆናቸው መረጃ ደርሶናል” ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ስለጉዳዩ መረጃ እንደደረሳቸው የተናገሩት የኦነግ ሥራ አስፈፃሚ አባልና ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ “ድርጊቱ የተፈፀመው ‘በኦነግ ሠራዊት ነው፤ አይደለም’ የሚለውን በማጣራት ላይ ነን” ብለዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5
በአማሮ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች ጥቃት እንዳደረሱ የወረዳው አስተዳዳሪ ገለፁ