በአሁኑ ሰዓት በተለይ በግብር አተማመን የተነሳ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ቅሬታ በሁሉም ቦታዎች አለ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በአሁኑ ሰዓት በተለይ በግብር አተማመን የተነሳ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ቅሬታ በሁሉም ቦታዎች አለ።
ከዚያ ውጭ ግን አሁን ትንሽ ጠንክሮ የወጣው እስካሁን ባለን መረጃ ምሥራቅ ጎጃም ላይ ሸበል በረንታ፣ ብቸና፣ ደብረ ወርቅ፣ ረቡዕ ገበያ ወይም ስናን ወረዳ፣ መርጦ ለማሪያም፣ ሞጣ ቀራንዮና ፈለገ ብርሃን ወረዳዎች እነዚህ በሙሉ በዛሬው ዕለት የንግድ ድርጅቶች ተቋርጠው ነው የዋሉት።
በቅርቡ በመንግሥት የተጣለውን ግብር ግምት በመቃወም በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች በዛሬው ዕለት የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው መዋላቸውን በአካባቢዎቹ የሚንቀሳቀስ አንድ የፖለቲካ ድርጅት አመለከተ።
መንግሥት እየወሰደ ያለውም እርምጃ ለችግሩ መፍትሄ የሚያስገኝ አይደለም ሲል ተችቷል።
በርካታ የንግድ ድርጅቶች ባለቤቶች የታሰሩባትን የባሕር ዳር ከተማ ጨምሮ በተባሉት ከተሞችና አካባቢዎች በዛሬው ዕለት ያለውን ሁኔታ ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የገለጡት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ዋና ፀሐፊ እና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አዳነ ጥላሁን ናቸው።
Your browser doesn’t support HTML5