በአማራና በኦሮሚያ- የተከሰተው አድማ

(ፎቶው፡ በባህርዳር ከተማ በዛሬው ዕለት ሲሆን ከባሕርዳር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገፅ ላይ የተገኘ ነው)

በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የንግድ ቤቶችና የሕዝብ ትራንስፖርት ተቋማት አገልግሎት ማቋረጣቸውን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው። ለዚህም በምክንያትነት የሚያስቀምጡት በባሕርዳር ከተማ የዛሬ ዓመት በተቃውሞ ወቅት በፀጥታ አካላት የተገደሉ ወጣቶችን ለማስታወስና አሁን በአማራ ክልል ተግባራዊ መደረግ የጀመረውን የቀን ገቢ ግምት በመቃወም ነው። በኦሮሚያ ደግሞ የታሰሩ የፖሊተካ አመራሮች ይፈቱ የሚል እና በቀን ገቢ ግምቱ ላይ መፍትሔ አልተሰጠንም የሚል ይገኝበታል።

ጽዮን ግርማ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎችን አነጋግራ ተከተያዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራና በኦሮሚያ- የተከሰተው አድማ

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።