ህዝቡ ራሱ ታግሎ ያመጣውን ሰላምና ነፃነት ወደ ኃላ እንዳይቀለበስ ከመንግሥት ጎን ሊቆም ይገባል ሲል የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ገለፀ።
ባህር ዳር —
ህዝቡ ራሱ ታግሎ ያመጣውን ሰላምና ነፃነት ወደ ኃላ እንዳይቀለበስ ከመንግሥት ጎን ሊቆም ይገባል ሲል የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ገለፀ። የፅ/ቤቱ አዲሱ ተሿሚ አቶ አሰማኸኝ አስረስ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አመሻሹን መግለጫ ሰጥተዋል።
መግለጫዎቹ ካተኮሩባቸው ነጥቦች ውስጥ ሰላምና ፀጥታ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይ በትላንትናው ዕለት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ በተከሰተው ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ በርካታ ንብረቶችም ወድመዋል።
ሁከቱን ፈጥረዋል የተባሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር የማዋሉ ሥራ የተጀመረ ሲሆን የፀጥታ ኃይሎችም አካባቢውን የማረጋጋት ሥራ እየሰራ መሆኑን ኃላፊው በመግለጫቸው አትተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5