ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ለፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደብዳቤ ፃፉ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ዩናይትድ ስቴትስ በልማትና በሰብዓዊ ዕርዳታ መልክ ለአፍሪካ አምባገነኖች በየዓመቱ የምትሰጠው በቢሊዮኖች ዶላሮች የሚገመት የገንዘብ ዕርዳታ በሙሰኞች ስለሚባክን መቆም አለበት ሲሉ በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሳንበርናንዲኖ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የሕግ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደብዳቤ ፅፈዋል።

ከግብር ከፋይ አሜሪካውያን እየተሰበሰበ የሚላከው ገንዘብ ለታቀዱ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያነት ስለማይውል መቆም አለበት ብለዋል፣ ደብዳቤውን ለፕሬዚዳንት ትራምፕ የላኩት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም በተለይ ኢትዮጵያን አስመልክቶ በፃፉት ደብዳቤ፡፡

በፃፉት ደብዳቤ ይዘትና ዓላማ ዙሪያ፣ የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያምን አነጋግሯቸዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5