በራያ አላማጣ ወረዳ አዋሳኝ ግጭት አስተዳደሩ እና የትግራይ ክልል ተካሰሱ

Your browser doesn’t support HTML5

በራያ አላማጣ ወረዳ አዋሳኝ ግጭት አስተዳደሩ እና የትግራይ ክልል ተካሰሱ

የትግራይ ክልል ታጣቂ ኀይሎች ወደ ራያ አላማጣ ወረዳ በመግባት አንድ ቀበሌ መቆጣጠራቸውን፣ የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አስታወቁ።

ከንቲባው ኀይሉ አበራ፣ ታጣቂዎቹ በቀበሌዋ የሚገኙትን ጎጦች ለመቆጣጠር ወሰዱት ባሉት ጥቃት ሲቪሎች መገደላቸውን፣ የአካል ጉዳት መድረሱንና ተቋማት መዘረፋቸውን ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ረዳኢ ኃለፎም በበኩላቸው፣ ውንጀላውን አስተባብለዋል፤ በአንጻሩ ከራያ አላማጣ ወረዳ በኩል ትንኮሳ ተፈጽሞ እንደነበርና እርሱንም መመከት እንደተቻለ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል።

ሁለቱም አካላት፣ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዳይተገበር ፍላጎት አላቸው፤ በሚል እርስ በርስ ይካሰሳሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።