የጦርነት ተፈናቃዮች ወደ ራያ አላማጣ እና አካባቢው በመመለስ ላይ ናቸው

የኢትዮጵያ ካርታ

  • በአላማጣ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደሩ የትግራይ ክልልን ወቅሷል

የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት ተከትሎ ከራያ አላማጣ እና ከራያ ባላ ወረዳዎች እንዲሁም ከአላማጣ ከተማ ተፈናቅለው ነበር የተባሉ ሰዎችን የመመለስ ሥራ መጀመሩን፣ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የደቡባዊ ትግራይ ዞን አስታወቀ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የጦርነት ተፈናቃዮች ወደ ራያ አላማጣ እና አካባቢው በመመለስ ላይ ናቸው

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ፣ “ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ውስጥ ከ15ሺሕ የሚበልጡ ተፈናቃዮችን መመለስ ተችሏል፤” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

ከጦርነቱ ፍጻሜ በኋላ በዐማራ ክልል የተቋቋመው የአላማጣ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር በበኩሉ፣ በትግራይ ክልል በኩል እየተወሰደ ያለው ርምጃ፣ “ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ያፈነገጠ ነው፤ ከጦርነቱ በኋላ በተፈናቃይ ስም እየተመለሱ ያሉት የህወሓት ታጣቂዎች ናቸው፤” በማለት ተቃውሞ አሰምቷል፡፡