በመንበረ ሰላማ ተፈጸመ ያሉትን ሹም ሽረት ያልተቀበሉ የአላማጣ ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰሙ

Your browser doesn’t support HTML5

በመንበረ ሰላማ ተፈጸመ ያሉትን ሹም ሽረት ያልተቀበሉ የአላማጣ ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰሙ

በትግራይ የተቋቋመውና “መንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት” ተብሎ የሚጠራው ተቋም፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርአት ውጭ በሆነ መልኩ በራያና አካባቢው የራሱን አስተምህሮና አስተዳደራዊ ስርአት በመዘርጋት ላይ ነው ያሉ የአላማጣ ከተማ ኗሪዎች ተቃወሟቸውን ትናንት በሰላማዊ ሰልፍ ገለጹ፡፡

በአካባቢው ያሉት አብያተክርስቲያናት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ስር እንደቆዩ የሚናገሩት የራያና አካባቢው አገረስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን ሃፍቱ አየነ፣የመንበረ ሰላማ ቤተክህነት ነባሩን መዋቅር በማፍረስ፣ በራያና አካባቢው በሚገኙ አምስት ወረዳዎች ስራ አስኪያጆችን ጨምሮ 20 የሚደርሱ ሰዎችን ሾሟል በማለት ከሰዋል።

ስለ ሹመቱ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው የገለጹት የመንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ ብጹእ አቡነ አረጋዊ፣ አካባቢው ከጦርነቱ በፊት በትግራይ ክልል ሲተዳደረር የነበረ በመሆኑና የተፈናቀለውም ሰው ወደ ቀየው በመመለሱ፣ መተዳደር ያለበት በመንበረ ሰላማ የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቤተክህነት ስር ነው ብለዋል፡፡