ቡሩንዲ ውስጥ የረድዔት ድርጅቶች

  • ቪኦኤ ዜና
ቡሩንዲ ውስጥ ሰብአዊ መብት እየተረገጠ ነው የሚል ሥጋት በሚሰማበት በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ መንግሥት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለማገድ መወሰኑን የረድዔት ድርጅቶች እያወገዙ ነው።

ቡሩንዲ ውስጥ ሰብአዊ መብት እየተረገጠ ነው የሚል ሥጋት በሚሰማበት በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ መንግሥት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለማገድ መወሰኑን የረድዔት ድርጅቶች እያወገዙ ነው።

የቡሩንዲ የብሄራዊ ፀጥታ ካውንስል ያስተላለፈው ውሳኔ የድንበር አልባ ሀኪሞችን፣ የካቶሊክ የረድዔት አገልግሎትን የመሳሰሉት የሥራ እንቅስቃሴን ያቆማል። እነዚህ ሁለት ድርጅቶች በሀገሪቱ ተደራሽነት ለሌላቸው ሰዎች ወሳኝ የህክምና አገልግሎት ሲሰጡ እንደቆዩ ተገልጿል።

"እነዚህ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመንግሥት የማይቀርቡትን የህክምናና የትምህርት አገልግሎቶችን በመሸፈን ለህዝቡ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ናቸው" ሲሉ ኒኮላስ አጎስቲኒ አስገንዝበዋል።

አጎስቲኒ በምስራቅ አፍሪካ ላሉት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የቆመ ኡጋንዳ ያለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ ናቸው።