አዲስ አበባ —
ከሽብር ተግባር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በእስር ላይ ከነበሩት ሁለት የአሐዱ ራዲዮ ጋዜጠኞች አንዷ መፈታቷ ተገለጸ።
የአሐዱ ራዲዮ 94.3 ጋዜጠኛ ሉዋም አታክልቲ ዛሬ በዋስ መፈታቷን ጠበቃዋና የምትሠራበት ተቋም ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቀዋል። ሌላው የጣቢያው ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁም በዋስ እንዲለቀቅ ፍ/ቤት መወሰኑ ታውቋል፡፡
ሁለቱን ጋዜጠኞች "ከሽብርተኛ ድርጅት ተልዕኮ በመቀበል እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርተዋል" በሚል ጥርጣሬ ከሳምታት በፊት በቁጥጥር መዋላቸው ይታወሳል፡፡
የሕግ ጠበቃቸውንና የጣቢያውን ኃላፊ በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግረናል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
በእስር ላይ የነበረችው የአሐዱ ጋዜጠኛ ተፈታች