የስዊድኑ አካዳሚ ባጋጠመው የወሲብና የገንዘብ ቅሌት፣ ለስነ ጽሑፍ ያዘጋጀውን የ2018 የኖቤል ሽልማት ለሌላ ጊዜ ማስተለፉ ተገለፀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የስዊድኑ አካዳሚ ባጋጠመው የወሲብና የገንዘብ ቅሌት፣ ለስነ ጽሑፍ ያዘጋጀውን የ2018 የኖቤል ሽልማት ለሌላ ጊዜ ማስተለፉ ተገለፀ።
አሸናፊዎችን የሚመረጠው አካዳሚ ዛሬ ዐርብ ይፋ ባደረው መግለጫ እንደታወቀው፣ የ2018 ተሸላሚዎች፣ ሽልማቶቻቸውን በመጪው እአአ 2019 ያገኛሉ። ከፍተኛ እውቅና ያለው ይኸው ድርጅት ውሳኔውን ይፋ ያደረገው ባለፈው ሳምንት ስቶክሆልም ውስጥ ባደረገው ስብሰባ መሆኑም ታውቋል።
ቀጣዩ ሎሬት ይፋ ከመደረጉ አስቀድሞ፣ ሕዝባዊ አመኔታን እናገኝ ዘንድ ጥቂት ጊዜ መውሰድ ግድ ብሎናል ሲሉ፣ የአካዳሚው ቋሚ ዋና ፀሐፊ አንደርስ ኦልሰን ተናግረዋል።