የአፍሪኮም አዛዥ በሶማሊያ ስለ አሜሪካ ጦር ተሳትፎ ግልፅ አደረጉ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ በአፍሪካ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ማይክል ላንግሊ

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪኮም አዛዥ በሶማሊያ ስለ አሜሪካ ጦር ተሳትፎ ግልፅ አደረጉ

የአፍሪካ ህብረት እኤአ በሚቀጥለው 2025 አዲስ ለሚያሰማራው የሶማሊያ ድጋፍ ሰጪ እና እና አረጋጊ ተልዕኮ (AUSSOM) የትኞቹ ሀገራት ወታደር እንደሚያዋጡ ገና አልወሰነም።

የሶማሊያ መንግሥት ኢትዮጵያን ከሶማሌላንድ ጋር ባደረገችው አወዛጋቢ ሥምምነት የተነሳ ከተልዕኮው እንድትገለል በመጠየቁ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የዘገየ ይመስላል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የተካረረው ውዝግብ ሳይበርድ በቀጠለበት በዚህ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ በዚህ ዓመት መጨረሻ በሚደረገው የአፍሪካ ህብረቱ የሶማሊያ ተልዕኮ ሽግግር እንደማትሳተፍ በአፍሪካ የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ማይክል ላንግሊ አስታውቀዋል፡፡

በአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢዎች በካርላ ባብ እና ሃሩን ማሩፍ የተሰናዳው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡