የአፍሪካ አገሮች ከኃይላን ጋር ማበርም ሆነ የመጋፈጥ መርህ

  • ቪኦኤ ዜና
ሩሲያን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለማስወጣት በተጠራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ድምፅ አሰጣጥ ላይ የተሳተፉ ሃገሮች ኒው ዮርክ እአአ ሚያዝያ 7/2022

ሩሲያን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለማስወጣት በተጠራው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ድምፅ አሰጣጥ ላይ የተሳተፉ ሃገሮች ኒው ዮርክ እአአ ሚያዝያ 7/2022

አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ዩናይትድ ስቴትስ መር በሆነው የፀረ ሩሲያ ውግዘት ላይ ተካፋይ ባለመሆን በተደጋጋሚ ገለልተኛ ሆነው መቆየታቸው ከኃይላን አገሮች ጋር የማበርም ሆነ የመቃወም እንቅስቃሴ ማድረግ የማይፈግሉ አገሮች ቡድን (Non-Aligned Movement- NAM ) በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ውስጡን እየተንቀሳቀሰ ስለመሆኑ ፍንጭ ይሰጣል ሲሉ ተንታኞች ተናግረዋል፡፡

120 አገራት የነበረው ይህ ቡድን፣ ከኃያላን አገሮች ጋር በይፋ ማበርም ሆነ መላተሙን እንደማይፈቅድ በመርኃ ደረጃ ሲያሰማ ቆየቷል፡፡ እአአ የካቲት 24 ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች አንስቶ በጠቅላላው የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ ሁለቱ አሳሪ ያልሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

የመጀመሪያውን ገሚሶቹ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ወይም ትልቋን የአውሮፓ አገር ከማውገዝ ድምፃቸውን ይዘዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያን ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አግዷታል፡፡

በዚህ ውሳኔ ካልተሳተፉት 58 አገሮች መካከል 24ቱ የአፍሪካ አገሮች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ ይገኙበታል፡፡ ስምንት የአፍሪካ አገሮች አልጄሪያ ኢትዮጵያ ዚምባቡዌና ውሳኔውን ተቃውመው ድምፅ ከሰጡት ውስጥ ናቸው፡፡

ፓወሊን ባክስ የዓለም አቀፍ የቀውስ ቡድን የአፍሪካ ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር እንደሚሉት “የአፍሪካ አገሮች በግጭቱ የተነሳ በአህጉሩ በጨመረው የምግብና ነዳጅ ዋጋ በጣም ሰግተዋል፡፡ ሩሲያን በማውገዙ ጉዳይ ተሳታፊ አለመሆናቸው በዓለም አቀፍ አካላት ምንም ማድረግ አለመቻል ደስተኛ አለመሆናቸውን ያመልከታል፡፡”

ባክስ ለቪኦኤ ስለዚሁ የአፍሪካ አገሮች አቋም ሲናገሩ “በዚህ ጦርነት ምንም ዓይነቱ ወገናዊነት እንደማያሳዩ የሚገልጹበት መንገድ ነው በተለይ ደግሞ በዩናይትድ ስቴትስና በምስራቁ ዓለም መካከል ቀዝቃዛው ጦርነት ቢካሄድ” ብለዋል፡፡

በለንደን የሚገኙ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ ፓወል ኢጂሜ በበኩላቸው “ሉዓላዊ የሆነ የአገር ጥቅምን ለመከላከል መሞከርና እንዲሁም ከሩሲያ ጋር ያለ የሁለትዮሽ ግንኙነት ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ለምን ድምጽ ከመስጠት እንደተቆጠቡ ያስረዳል፡፡” ብለዋል፡፡

“የተባበሩት መንግሥታት ለአፍሪካ ትልቁን ድምጽ ልትስጥ ይገባል” ያሉት ኢጂሜ “አፍሪካ አህጉርን የተሰራቸው ከ54 አገሮች ነው ይሁን እንጂ ግን እንደ አጋር በእኩል ዐይን የሚታዩ አይደሉም” ብለዋል፡፡

መሠረቱን ኒው ዮርክ ያደረገው የሱፋን ማዕከል ሥራ አስፈጻሚ ድሬክተር፣ ናውሪን ቾዎድኸሪ ፊንክ፣ “አብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች የረጅም ጊዜ ተቃዋሚም ሆነ ደጋፊ ያልሆነው ቡድን አባል በመሆናቸው ድምፅ ተአቅቦ ማድረጋቸው ምክንያት ያለው ትክክለኛ ምርጫ ነው” ብለዋል፡፡

ፊንክ ይህንን ሲገልጹ “የምግብ ደህንነት ዋስትናም ለብዙዎቹ አገሮች ቀዳሚው አሳሳቢ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ በኃያላኑ አገሮች ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ በጉዳዩ አለመነከር በተለይ ጣጣው አገር ውስጥ ላሉ ዜጎች የሚተርፍ ከሆነ የሚኖረው ተጽእኖ አሉታዊ ይሆናል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፓወሊን ባክስ ደግሞ ሲናገሩ “ተደጋጋሚ የሆነው ተአቅቦ ጽኑነትን ያሳያል፡፡” ብለዋል፡፡

አያያዘውም “በተለይ በሩሲያ ወይም የሩሲያ ሰዎች በሆኑ ላይ ጥገኛ የሆኑት ሰዎች ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ይጠቅማቸዋል፡፡ ለአንዳንዶቹ ተመልካቾች በተአቅቦው መግለጽ የሚፈልጉት ያለምንም ጥያቄና ችግር ምዕራቡን ዓለም ዝም ብለው የሚከተሉ አለመሆናቸውን ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ኢጂሜ የአፍሪካ አገሮች በተባበሩት መንግሥታት ድምፃቸው ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያስተላለፉት

“ጦርነትን በሌላ ጦርነት ማሸነፍ የማይቻል መሆኑን” ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአፍሪካ አገሮች ለሩሲያው የዩክሬን ወረራ የሰጡት ምላሽ ዩክሬንን ከመደገፍ የኔቶን ምላሽ እስከማውገዝ የሚሄድ መሆኑን ጋሉፕ የህዝብ አስተያየት ድምፅ ማሰባሰቢያ አመልክቷል፡፡

በዚህም መሰረት ባላፈው ዓመት የሩሲያን አመራር በመደገፍ ከአፍሪካ የተሰጠው አማካይ አስተያየት አምና 42 ከመቶ ሲሆን ይህ ሌላው ዓለም ከሰጠው 33 ከመቶ ከፍ ያለ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ግን ከአፍሪካ አገሮች የተገኘው ድምፅ ለዩናትይትድ ስቴትስ 60 ከመቶ፣ ለቻይና 52፣ ከመቶ ለጀርመን 49 ከመቶ፣ ሲሆን ለሩሲያው አመራር የተሰጠው ይሁንታ ከዚህ ያነሰ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የጋሉፕ የህዝብ አስተያየት ድምፅ እንደሚያሳየው አፍሪካውያን ለሩሲያ ያላቸው በጎ አመለካከት የተንጸባረቀበት እኤአ 2011 በነበረው 57 ከመቶ ላይ መቆሙ ተገልጿል፡፡