አፍሪካ ተወርዋሪ ጦር ሊኖራት ነው

ሃያ አምስት ሺህ ሠራዊት የሚኖረው የአፍሪካ ተጠባባቂ ጦር በጥቂት ወራት ውስጥ ለግዳጅ ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ሃያ አምስት ሺህ ሠራዊት የሚኖረው የአፍሪካ ተጠባባቂ ጦር በጥቂት ወራት ውስጥ ለግዳጅ ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ይህ ተጠባባቂ ጦር አፍሪካ የውጭ ጣልቃገብ ጦር ላይ የመመርኮዟን ነገር ለመቀነስና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ጊዜ ሳይባክን ፈጥኖ መወርወር የሚችል ኃይል ለማዘጋሀጀት የታሰበ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ወደ ተግባር መግባቱ የመናገሩን ያህል ቀላል አይደለም እየተባለ ነው፡፡

ጦሩ በአምስት ብሪጌዶች የሚደራጅና በኅብረቱ በቀጥታ የሚታዘዝ እንደሆነም ታውቋል፡፡

የዚህ በመጭው የአውሮፓ 2016 ዓ.ም መጀመሪያ ሥራ ይጀምራል የተባለ ኃይል አንድ ጋንታ ‘አማኒ አፍሪካ - ሁለት’ ተብሎ የተጠራ ወታደራዊ ልምምድ ሰሞኑን ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያካሄደ ሲሆን ሃሣቡ ብዙ የከበዱ ፈተናዎች ከፊቱ ቢኖሩም ተግባራዊ ለማድረግ ግን የሚቻል መሆኑን የልምምዱ ቃል አቀባይ ደቡብ አፍሪካዊ የባሕር ኃይል አባል ሻምበል ያኩ ቲኒሴን አመልክተዋል፡፡

ዋናው እክል ሊሆን የሚችለው የገንዘብ እጥረት ሲሆን ሌላው ግን የሚሠማራው ጦር ወታደሮች በእውኑ ገለልተኛ ሊሆኑ ይችላሉ ወይ የሚል ጥርጣሬ በሚሠማራባቸው ሃገሮች ውስጥ ሊነሣ የመቻሉ ጉዳይ መሆኑን አንድ ተንታኝ ጠቁመዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

አፍሪካ ተወርዋሪ ጦር ሊኖራት ነው