በሊቢያ ሰሜናዊ የባሕር ወደብ፣ ቢያንስ ሰባ አራት የአፍሪካውያን ፍልሰተኞች አስከሬን ማግኘቱን፣ የሊቢያ ቀይ ጨረቃ ዛሬ ማክሰኞ አስታወቀ።
በሊቢያ ሰሜናዊ የባሕር ወደብ፣ ቢያንስ ሰባ አራት የአፍሪካውያን ፍልሰተኞች አስከሬን ማግኘቱን፣ የሊቢያ ቀይ ጨረቃ ዛሬ ማክሰኞ አስታወቀ።
የቀይ ጨረቃ ቃል አቀባይ ሞሐመድ አል ሚስራቲ እንዳስታወቁት፣ ትናንት ሰኞ በሜዲትሬንያን ወደብ በምትገኘው ዛዊያ ከተማ አካባቢ አንዲት የተበሳሳች ጀልባ ተገኝታለች። እንዲህ ዓይነቷ ጀልባ ደግሞ እስከ አንድ መቶ ሃያ ሰዎችን ስለምትጭን፣ ምናልባትም ከተጠቀሱት ሰባ አራት በላይ የፍልሰተኞች አስከሬን ሊገኝ እንደሚችል፣ ቃል አቀባዩ አል ሚስራቲ ገልፀዋል።
አስከሬኖቹ፣ ትሪፖሊ ውስጥ ወደሚገኘውና ማንነታቸው የማይታውቁ ሰዎች ወደሚያርፉበት መካነ መቃብር እንደሚወሰድ፣ አል ሚስራቲ ጨምረው ገልፀዋል።