የአፍሪካ መራብና የዓለም ምላሽ

ፎቶ ፋይል

በመጭዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ “ከሃያ ሚሊዮን በላይ ቁጥር ያለው ሰው አፍሪካ ውስጥ ለበረታ ረሃብ ወይም ቸነፈር ይጋለጣል፤” - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ናቸው ይህንን ክፉ ዜና ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት፡፡

በመጭዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ “ከሃያ ሚሊዮን በላይ ቁጥር ያለው ሰው አፍሪካ ውስጥ ለበረታ ረሃብ ወይም ቸነፈር ይጋለጣል፤” - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ናቸው ይህንን ክፉ ዜና ሰሞኑን ይፋ ያደረጉት፡፡

ጉቴሬዥ የከትናንት በስተያው ዓርብ ጄኔቫ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ዛሬ ያለውን ሁኔታ “እጅግ አሳሳቢና አስጊ ነው” ብለውታል፡፡

“በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች - አሉ ጉቴሬዥ - ዛሬ እየኖሩ ያሉት በረሃብና በሞት መካከል፤ ለበሽታዎችና ለወረርሽኞች ተጋልጠው ነው፡፡”

በተለይ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ የመንና የናይጀሪያ ሰሜን ምሥራቅ አካባቢዎችን - “የቸነፈር ቀጣና” ሲል አውጇል የመንግሥታቱ ድርጅት፡፡ በተለይ የደቡብ ሱዳን ዩኒቲ ጠቅላይ ግዛት ሁለት አውራጃዎች መቶ ሺኽ ሰው በቸነፈር መሰል ረሃብ እየተመታ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በመጭዎቹ አራት ሣምንታት ውስጥ ዓለም ካልተረባረበና ወደ አራት ቢሊዮን ተኩል ዶላር ካላሰባሰበ ይህ የደቡብ ሱዳን ሁኔታ ወደ ሌሎችም አካባቢዎች እንደሚዛመት ዋና ፀሐፊው አበክረወ ተናግረዋል - ትራጄዲ ነው ያለንበት ሁኔታ ብለዋል ጉቴሬዥ - የበረታ የሃዘን ገፅታ!

እስከያዝነው የአውሮፓ ዓመት - መጨረሻ ደግሞ ወደ 5.5 ቢሊዮን ያስፈልጋል፤ በዚህች ምድር ላይ ከሽብር ፈጠራ ባልተናነሰ ሁኔታ ሰቀቀንን እየዘራ ያልወን የረሃብና የተያያዥ በሽታዎች ሥጋት በተጠቀሱት አራት ሀገሮች ውስጥ ለመቆጣጠር፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ መራብና የዓለም ምላሽ