የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ስለ አሜሪካ ምርጫ ምን ይላሉ?

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፡- የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት የሪፐብሊካን ፓርቲው እጩ ዶናልድ ትረምፕ እና የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ካመላ ሄሪስ

Your browser doesn’t support HTML5

የአፍሪካ ዲያስፖራዎች ስለ አሜሪካ ምርጫ ምን ይላሉ?

ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ኻሪስ ወደ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ከመግባታቸው በፊት፣ ከዩናይትድ ስቴትስ መራጮች ገሚስ ያህሉ በፕሬዝዳንት ባይደን እና በቀድሞ ፕሬዝዳንት ትረምፕ ደስተኛ እንዳልነበሩ ከህዝብ የተሰበሰቡ አስተያየቶች ያሳያሉ።

ያሳለፍነው ሚያዚያ ወር ላይ፣ በዚህ ምርጫ ድምፃቸውን መስጠት እንደማያስቡ የገለጹልን አንድ የአፍሪካ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ አባል አነጋግረን የነበረ ሲሆን፣ የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ጄፍ ስዊኮርድ በቅርቡ በድጋሚ አግኝቷቸው፣ የካማላ ኻሪስ እጩ መሆን ውሳኔያቸውን እንደገና እንዲያጤኑት አድርጓቸው እንደሆነ ጠይቋቸዋል።