"አፍሪካ የተፈጥሮ ጋዟን የመጠቀም መብት አላት" - የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

  • ቪኦኤ ዜና
የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዋሚ አዴሲና

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዋሚ አዴሲና

ምንም እንኳ አንዳንድ የCOP27 አባል አገራት በአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የተፈጠሮ ጋዝ መጠቀም እንዲያበቃ ግፊት ቢያደርጉም አፍሪካ ግን የተፈጥሮ ጋዝዋን ልትጠቀም ይገባታል ሲሉ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዋሚ አዴሲና ተናገሩ፡፡

ፕሪዚዳንቱ በCOP27 አባል አገራት የአየር ንብረት ጉባኤ በሚደርስበት ማናቸውንም ንግግሮች ላይ የአፍሪካ አገሮች የተፈጠሮ ጋዛቸውን የመጠቀም መብታቸው ሊንጸባረቅ ይገባል ብለዋል፡፡

በቅሪተ አካሎች የሚመነጨው የተፈጥሮ ጋዝ በአየር ንብረት ሥምምነቱ ቁልፍ መነጋገሪያ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ህንድን ጨምሮ አንዳንድ አገሮች የተፈጥሮ ጋዝን መጠቀም ለመቀነስ ማሰባቸውን ደረጃ በደረጃ ለመቀነስ አስበዋል፡፡

“አፍሪካ ግን የኃይል አቅርቦትን ለማመጣጠን የተፈጠሮ ኃይልን መጠቀም ያስፈልጋታል” ያሉት የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት

“አፍሪካ ኃይል ለማመንጨት ሁሉንም የተፈጥሮ ጋዝዋን የምትጠቀም እንኳ ቢሆን በልቀቱ ሊኖራት የሚችለው ድርሻ 0.67 ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ስለዚህ አፍሪካ የታዳሽ ኃይሏን ለሟሟላት የተፈጥር ጋዝ ሊኖራት ይገባል፡፡ ይህ የኃይል አቅርቦት ተደራሽነት ተመጣጣኝ ዋጋ እና ደህንነትን ለማረጋገጥ ይረዳታል” ብለዋል፡፡

ዓለም በመከካለኛው አጋማሽ ክፍለ ዘመን የዓለም ሙቀትን ወደ 1.5 ዲግሪ ሲልሼየስ ዝቅ ለማድረግ አስቀምጣ የነበረውን ግብ ማሳካት በማትችልበት ሁኔታ ላይ የምትገኝ መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

በዚህ የተነሳም የጉባኤው አንዱ ትኩረት አገሮች የታዳሽ ኃያልን እድገት ማፋጠን ወደ የሚቻሉብት ደረጃ ስለማሸጋገር እንደሆነ በዘገባው ተገልጿል፡፡