የመታቀፍ አገልግሎት በደቡብ አፍሪካ እያደገ ነው

  • ቪኦኤ ዜና
ፕሮ ከድሊንግ የተባለ የማቀፍ አገልግሎት ኩባንያ መስራች ፍሎረንስ ሌትሰዋሎ

ፕሮ ከድሊንግ የተባለ የማቀፍ አገልግሎት ኩባንያ መስራች ፍሎረንስ ሌትሰዋሎ

በደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቱ የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ሰዎችን የማቀፍ አገልግሎት የሚሰጡ የንግድ ቤቶች በመስፋፋት ላይ ይገኛሉ፡፡

አገሪቱን በከባድ የመታው የኮቪድ 19 ወረሽኝ እና ባለው የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ሰዎች የብቸኝነት ስሜት እያጠቃቸው በመሆኑ የመታቀፍ አገልግሉቱ መስፋፋቱን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

የቪኦኤው ዛሂር ቃሲም ከጆሃንስበርግ እንደዘገበው አንዳንዶች ጉዳዩ ግራ ቢያገባቸውም፣ የመታቀፍ አገልግሎቱ ግን ታዋቂነትን እያገኘኛ እየተስፋፋ ነው፡፡

ፕሮ ከድሊንግ የተባለ የማቀፍ አገልግሎት ኩባንያ ባለቤት ለቪኦኤ እንዳሉት ሥራው ገንዘብ ለማግኘት የሚፈጸም ቢሆንም፣ ዋናው ጉዳይ ግን ‘ኡቡንቱ’ ወይም ወንድማማችነትንና ለሌሎች ሰብዓዊነት ማሳየትን የሚያበረታታውን አፍሪካዊ እሴት ማጎልበት ነው፡፡

እንዲህ ዓይነቱ ሕክምና የኡቡንቱን እሴት ያበለጽጋል ሲሉ የሥነ ልቦና ባለሞያ የሆኑት አኔሊ ሲሲዋና ለቬኦኤ ተናግረዋል፡፡

በአሜሪካ ሙያዊ የመታቀፍ ሕክምና አገልግሎት መሰጠት የተለመደ ነው፡፡